8.1 በSatellite Finder መፈለግ
Satellite Finder ዲሽን ትክክለኛ ሳተላይት ላይ ለማስመራት ይረዳል።
እርምጃዎች፦
Finder ከLNB እና Receiver መካከል ያገናኙ
Receiver እና TV አብራ
ዲሽን በቀስታ ግራ–ቀኝ አንቀሳቅስ
Finder ሲጮህ / Signal ሲጨምር ቁም
Elevation ትንሽ አስተካክል
👉 ከፍተኛ ድምፅ ≠ ትክክለኛ ሳተላይት።
👉 Receiver menu ላይ ያረጋግጡ።
8.2 በReceiver መፈለግ (Manual Way)
Finder ከሌለ፣ Receiver ብቻ መጠቀም ይቻላል።
Menu → Installation → Satellite Setup
ሳተላይት ምረጥ (Nilesat)
Transponder ጨምር (Known TP)
Signal bar ክፈት
ዲሽ በቀስታ አንቀሳቅስ
👉 Quality 0% → አቅጣጫ ተሳስቷል ወይም
እያገኘኸው አይደለም ማለት ነው።
8.3 Transponder (TP) ምንድነው?
Transponder ሳተላይት ላይ ያለ የምልክት መስመር ነው።
TP ይዟል፦
Frequency
Symbol Rate
Polarization
ምሳሌ (Nilesat):
11747 H 27500
8.4 Signal Strength እና Quality ማስተካከል
Strength ብዙ ጊዜ አይቀንስም
Quality ≥ 60% → ጥሩ
Quality ≥ 75% → በጣም ጥሩ
ለማሻሻል፦
ዲሽ ትንሽ ትንሽ አንቀሳቅስ
LNB Skew አስተካክል
Bolt በመጨረሻ ጠንክር
8.5 የተሳካ ምልክት ማረጋገጥ
2–3 Transponder ተመልከት
Quality አንድ አይነት ከሆነ ዝግጁ ሆኗል